top of page


ከአስተዳደር ጉባዔ ማስታወቂያ
በጌታ የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችሁም ይሁንላችሁ።
ባለፈው ሳምንታት በነበሩን ተከታታይ ፕሮግራሞች እና ባለፈው ሳምንት በነበረው ስለ ሀገራችን ድንገተኛ የፀሎት ጥሪ ስለ ቃተታችሁት እና ስላደረጋችሁት መሰጠት ሁሉ ጌታ አብዝቶ አብዝቶ ይባርካችሁ::
ነገ ሊኖረን የሚገባ የነበረው መደበኛው የውራዊ ፀሎት ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት ለሀገራችን በወቅቱ እንድንፀልይ የፀሎት ፕሮግራሙን ወደፊት ስላመጣነው ነገ የፀሎት ፕሮግራም ስለማይኖር መጥታችሁ እንዳትደክሙ ላልሰሙም ወገኖችም እንድታሰሙልን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን::
ከቤተ ክርስቲያናችን ተልዕኮዎች ከሆኑት ፕሮግራሞች አንዱ ቅዳሜ በ30.11. 2019 የውሀ ጥምቀት ፕሮግራም እንድትገኙ እንዲሁም ጌታ የሰጠንን ሀላፊነት ለመፈፀም ቅዳሜ በ 14.12.2019 በቤተ ክርስቲያን ደረጃ የምንችል ሁላችንም ለወንጌል ስርጭት በፍራንክፍፈርት እና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ለመውጣት ስለምንፈልግ ከወዲሁ ፕሮግራማችሁን እንድታስተካክሉ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች::
ጌታ ይባርካችሁ!!
bottom of page