top of page

  • ደህንነት ማለት ምን  ማለት ነው 

  • ከምንድነው የዳነው ?

  •  ይሄ ደህንነት  ለማነው???

  •  የሚያድንስ ማነው ??

  •  ለመዳንስ ምን እናድርግ??

  •  ለምን  መዳን አስፈለገን? ?

እንግዲህ እነዚህን መሰረታዊ ሀሳቦችን እናነሳ አና በተለያየ ክፍል እንማማርባቸዋለን ።እንግዲህ ስለ ደህንነት መማር ያስፈለገን የተለያየ  አስተምህሮ ስላለ ነው ።እውነተኛውን ነገር ማወቅ ስለሚገባን ።በ ሐዋርያት ስራ 15/1ጀምሮ ስትመለከቱ ለጋ በነበረችው የ ክርስቶስ ቤ/ክ ውስጥ መሰረታዊ ረብሻ ያስነሳ ነገር ቢኖር ደህንነት የሚባለው ጉዳይ ነው ።ሀዋሪያትን ጉባኤ እንዲቀመጡ ያደረጋቸው ቁርጥ የሆነ ውሳኔ እንዲወስኑ ያደረጋቸው ሰለ ደህንነት የነበረው አስተምህሮ የተለያየ ስለነበረ ነው ። በ ሐዋርያት ስራ ም 15 እናንተ ከ 1ጀምሮ አንብቡት እኔ ከ22ጀምሮ  ልናገር ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። 

23 እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። 

24 ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው። ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ይህ ክፍል ቁጥር 1ላይ ሲናገር ደህንነት የሚጀምረው ከ ግርዘት ነው የሚል  አስተምህሮ ነበር ይሄ ደግሞ የ አይሁዶች ትምህርት ነበረ ፣በዛላይም የ አይሁዳውያን አላማኞችም ትምህርት ነበረ ።የተለያየ ተምህርት ተነስቷል ተዘርቷል ።እንግዲህ እቺን ለጋ ቤተክርስትያን ያጋጠመው

IMG-20190413-WA0024_edited.jpg

Habtamu  H/Yesus

Tel.017643871880

Email

IMG-20190413-WA0005_edited.jpg

Tekekel Bekele

Tel.017630114628

Email

bottom of page