የደንነት ትምህርት

                                ደንነት **የህያው ቃል ትርጉም በሀጢያቱ ምክንያት ወደ ፍርድ አይመጣም ይለዋል....ደህንንነት ያገኘ ሰው ሙሉ ዋስትና አለው **

ደህንነት >ማለት አንድ ሰው ክርስቶስ ኢየሱስን አዳኙና ጌታ አድርጎ ከዘላለም ሞት ወደ ዘላለም ህይወት በመሻገር አዲስ ህይወት መጀመር ማለት ነው፡፡

" በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"    (የዮሐንስ ወንጌል 3:16)

ደህንነት በአንድ ልጁ በኩል እንዲያው ያለ መስፈርት የሚፈፀም መዳን ብቻ ሳይሆን አለምጥፋትም የሞላበት ነው፡፡

ምክንያቱም እንዲድን እንጂ እንዳይጠፋ ስለሚል

ወንጌል ማለት፡- መዳን + አለመጥፋት= የዘላለም ህይወት ነው፡፡


ደህንነት አግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰራው ስራ_እንጂ_ሰዎች_ለእግዚአብሔር_የሚሰሩት_ወይም_የሰሩት_አይደለም ፡፡


በደህንነት ስራ ውስጥ እግዚአብሔር በክርስቶስ ብቻ ሰዎችን ወደ ዘላለም ህይወት ጠርቷል...

" እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።"


(የዮሐንስ ወንጌል 5:24)

የተጠራው ሰው ለጥሪው ምላሽን ሲሰጥ ማለት አሜን ብሎ ሲቀበል ሰውየው ባመነበት ቅፅበት ከዘላለማዊ ሞት ወደ ዘላለም ህይወት ይሻገራል እንደገናም ወደ ፍርድ አይመጣም።

ጥያቄ ካላችሁ በግል ፣ Tel:017643871880