Dienste der Gemeinde

Information

ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ከሚለው የ መፅሐፍ ቅዱስ መልክት ተከትላ ቤተክርስቲያናችን ይህን መልክት ይዛ ቅዱሳንን ወደ ትዳር ሕይወት እንዲአመሩ ታበረታታለች ::


መጀመሪያ አገልግሎት የሕይወት  መንገድ  ወቅታዊ ትዳር መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ልጆችን መባረክ አመሰራረት 



እውነተኛ  ደቀመዝሙር ማነው?

ደቀመዝሙር የሚለውን መጠሪያ ስንተረጉመው እውቀትን ለማግኘት አንድ የታወቀ አስተማሪ፣ መሪ ወይም ፈላስፋ ተከትለው ለሚሄዱ ሰዎች የሚሰጥ የመጠሪያ ስም   ነው፡፡ 


ለምሳሌ፡ የሙሴ ደቀመዝሙር፣  የዩሐንስ ደቀመዝሙር፣ የፈሪሳውያን ደቀመዝሙር፣  የኢየሱስ ደቀመዝሙር ፣ የእከሌ ደቀመዝሙር ወይም  . . . ደቀመዝሙር  ስለዚህ ደቀመዝሙር የሚለው  (ተማሪ፣ ተከታይ) ወይም ህይወቱን (ሁለተናውን) ለአንድ ለታወቀ ታላቅ ‹መምህር ወይም መሪ› የሰጠ  ሰውን ያመለክታል ማለት ነው፡፡ ደቀመዝሙር የህይወት ዘመን መሰጠትና መገዛትን የሚጠይቅ ነውና፡፡ 


በዚህች ዓለም የምንኖር ሁላችን አምነንና ተቀብለን ራሳችንን የምንሰጥለትና የምንገዛለት ማለትም ልንከተለው  "ደቀመዝሙሩ ልንሆን የምንወደው" በእኛ መነፅር  እኛነታችንን የነካ  የተሸለ አመለካከት ያለው ወይም እውቀት ያለው  የምንከተለው አለን፡፡ ትክክል ነው አይደለም  እርሱ ሌላ እራሱን የቻለ ጥያቄ ሆኖ!!

 እናም ራሳችንን ለሰጠንለት ለዛ  እውነተኛ ደቀመዝሙር  ወይም  ሐሰተኛ ደቀመዝሙር ሆነን መገለጣችን ግን አይቀሬ ነው፡፡ ሁለቱም የሚለዩት በህይወት አኗኗራቸው ነው፡፡ እኛነታችንን የሰጠንለት ‹ያ› በትምህርቱ እና ትምህርቱ በሚገልጥበት ኑሮ ህይወታችን ሲፈተሸ እውነተኛ ወይም ሐሰተኛ  ደቀመዝሙር ተብለን እንድንፈረጅ ያደርገናል፡፡ እናም የ . . . ደቀመዝሙር ነኝ ማለታችን የ . . . ን ሕይወት ወይም አመለካከት ሳንኖረው  ‹ የ . . . ደቀመዝሙርን ነኝ›  ወይም ‹ነው› በሚለው ቋንቋችን ብቻ  ልንሸፈነው አንችልም፡፡ 


እውነተኛ ደቀመዝሙርነት ፈለግን መከተል ብቻ ሳይሆን መሆንን ይጠይቃል፡፡  ደቀመዝሙርነት የግል እንጂ የጅምላ አይደለምና፡፡ ደቀመዝሙርነት ራስን የመካድ መንገድ እንጂ ራስን የመግለጫ መንገድ አይደለምና፡፡ ደቀመዝሙርነት በተራራ ላይ እንዳለ ከተማ መብራት መታወቂያ ያለው ማንነት እንጂ ድብስብስ የእንቅብ ውስጥ መብራት አይደለምና፡፡ ደቀመዝሙርነት በህይወት መዓዛችን ሌሎችን የምንስብበት እንጂ በክፉ ሽታችን የምናባርርበት አይደለምና፡፡



Sonntagsgottesdienst

MontagsGebet

Jugendgottesdienst

Youth Fellowship 

EVEnts

Angebote der gemeinde