13.04.2025
ቤተክርስትያን በዋናነት ወንጌልን አሁን ላለው ትውልድ ሆነ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና ሊኖራት ይገባል፣ በዚህ መሰረት ቤተክርስቲያናችን ለዚህ ራዕይ መሳካት የበኩላን ጥረት ታደርጋለች።በዚህም መሰረት ወጣቶች በሕብረት ውስጥ በመታቀፍ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን በማሳደግ አልፎም ከአለም ካሉ ግንኙነቶች ራሳቸውን በመጠበቅ በላቀ ሁኔታ ከክርስቲያን እህት ወንድሞቻቸው ጋር ህብረት በማድረግ ክርስቲያናዊ ህይወት በመካፈል ራሳቸውን በቤተክርስትያን ላለው አገልግሎት በማዘጋጀት ፀጋቸውን ለይተው ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ ብቁ እና ንቁ እንዲሆኑ ለማስቻል በተጨማሪም ተተኪ ትውልድን ማፍራት ዋነኛ እቅድ በማድረግ ይህን የህይወት እና የአላማ ለውጥ ለማምጣት ህብረቱ ከቤተክርስቲያን ስር ሆኖ የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ ለማስፈፀም ይሰራል።
የወጣት አዋቂዎች የፀሎት ህብረት ዘወትር ቅዳሜ ከ 18 ሰዓት ጀምሮ እንዲሁም በየ ሁለት ሳምንቱ እሁድ ከ 14 ሰአት ጀምሮ አብሮ ማዕድ በመቅመስ የአንድነት ጌዜን በማድረግ በአምልኮ እና በእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም በትምህርታዊ የዉይይት ግዜዎችን በማድረግ ያሳልፋል። በተጨማሪም በተለያዮ ተሳትፎዎች ወንጌል ስርጭት ፣ ጉዞ አብሮ በመሄድ ፣ የተለያዩ የባአላት እና የምስጋና ጌዜያትን በማድረግ የአንድነት ጌዜዎችን ያሳልፋል።