13.04.2025
እስካሁን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ለሚገኙ ተረጂዎች ከተደረጉት ድጋፍ መካከል:
- በተለያየ ህመም ላይ ለሚገኙ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
- ለአይን ስውራን:- ለአእምሮ ህሙማን:- በተለያየ በሽታ ለታመሙ ወገኖች:- ለአካል ጉዳተኞች:-ለህፃናት ህክምና
- አቅመ ደካሞችን በችግራቸው መርዳት
- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚገኙ ችግረኞች በችግራቸው መርዳት
- ለተለያዩ የክርስትና በዓላት ጊዜ ለወገኖች ድጋፍ ማድረግ:- ለአገልጋይ ቤተሰቦች የበዓል ድጋፍ ማድረግ
- በወንጌል ምክናያት ስደት ላይ ያሉ ወገኖችን ማገዝ
- ስራ ለመስራት አነስተኛ እና ጥቃቅን የሆነ ንግድ እንዲያቋቁሙ መርዳት (ለምሳሌ:- ሱቅ እንዲከፍቱ መርዳት:- የመንገድ ላይ ንግድ ለሚያደርጉ እናቶች እና እህቶች በአቅርቦት ማገዝ:- የዳቦ እና እንጀራ መጋገሪያ ምጣድ በመግዛት በዚህ ንግድ ላይ የሚተዳደሩትን እህቶች እና እናቶች መርዳት
- በገንዘብ እጥረት ምክናያት በትምህርታቸው እክል ያጋጠማቸውን ችግረኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተበረታትተው እንዲቀጥሉ እና እንዲጨርሱ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
- መድሃኒት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የመድኃኒት እርዳታ ማድረግ
- በገና በዓል ወቅት ከምእመናን እና ህፃናት በተሰበሰበ መዋጮ በሃገር ቤት በተለይም በቤተክርስቲያን ላሉ ችግረኛ ህፃናት እና ቤተሰቦቻቸው የገና በዓል ልዩ ስጦታ ማበርከት
በአሁን ወቅት (2025 ዓ.ም. መጀመሪያ ሩብ ዓመት) ምን እየተደረገ ነው?
- በወንጌል አገልግሎት እድሜያቸውን ሙሉ አገልግለው ለደከሙ አባቶች የገንዘብ ርዳታ
- በውድ አረጋውያን ማዕከል ላሉ አረጋውያን እናቶችና አባቶች በዓልን አስመልክቶ አዲስ አበባ ከሚገኘው ከውድ አረጋዊያን በጎ አድራጎት ጋር በመተባበር ለያንዳንዳቸው የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
- በሃረር ከተማ ለሚገኙ አረጋውያን ችግረኛ እናቶች የሚረዳቸው ለሌላቸው የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
የወደፊት እቅድ
- በቤተ ክርስቲያን ከእሁድ አምልኮ በኋላ የሚደረገውን የሻይ እና ቡና አገልግሎት በደንብ በማጠናከር በገቢው ችግረኞችን መርዳት
- ከቤተክርስትያን አባላት እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ከሆኑ ግለሰቦች የእርዳታና ርህራሄ አገልግሎት አባል እንዲሆኑ በማበረታታትና በየወሩ 5€ በመሰብሰብ የተለያዩ ችግረኞችን ለመርዳት መጣጣር
- ባሎቻቸው የሞቱባቸውን መበለቶች መርዳት:- የአካል ጉዳተኞችን መርዳት:- የተለያየ ህመም ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በተቻለ አቅም መርዳት:- በቤተሰብ አቅም ማነስ ምክናያት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በአግባቡ መቀጠል ያልቻሉትን የወደፊት ተስፋ ተማሪዎች በመለየት ድጋፍ ማድረግ
- ከላይ የተዘረዘሩትን እስካሁን እየተደረጉ ያሉትን እርዳታዎች አጠናክሮ መቀጠል