የተወሰደውን ማንነት ማስመለስ
የተወሰደውን ማንነት ማስመለስ
የተወሰደውን ማስመለስ በሚል ርዕስ በመጋቢ ታምራት ኃይሌ በፍራንክፈርት የሚገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ለ10 ቀናት ኮንፈረንስ ተካሂዷል ። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ጠቃሚ ከራሳቸው የብዙ አመት የአገልግሎት ልምድ ትምህርቶችን አግኝተናል። ይህ ኮንፈረንስ በተለይም ለቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለምእመናን ለመዘምራን እና ለገልግሎት መሪዎች የሆነ ስልጠና እና ማነቃቂያ ያቀፈ ነበር። መጋቢ ታምራት ኃይሌ በሚያቀርቡት ትምህርቶች ውስጥ የአገልግሎት መንፈስ፣ የመሪነት ትክክለኛ ራዐይ ፣ የመዘምራን ስልጠና እና መንፈሳዊ እድገት ጉዳዮች ተካተዋል። በዚህ ኮንፈረንሱ ተሳታፊዎችን በተግባራዊ ስልጠናዎች እና መጽሃፍ ቅዱሳዊ በሆነ መልኩ በማስተማር አገልግሎት እና መሪነት ላይ ያለውን አስተዋፅኦ ለማሳየት እና ለሁሉም አባላት ጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል።