13.04.2025
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ
መጋቢ እሸቱ ጉርሙ እባላለሁ:: የተወለድኩት በሰፕቴምበር 1952 ሲሆን በቀድሞ አጠራር በአርሲ ክፍለ ሐገር
ስሬ ከሚባል ከተማ አካባቢ በሚገኝ መንደር ነው:: እጅግ የምወዳት ባለቤቴ እመቤት አሩሲ በሞት የተለየችኝ
ሲሆን ጌታ ጽዮን እሸቱ፣ ሩት ጉርሙ እና ግሬስ ጉርሙ በሚባሉ ውድ ልጆች ባርኮኛል::
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በአርሲ ክፍለ ሐገር በአሰላ ከተማ የጨረስኩ ሲሆን፣ ከኩባ መንግስት የነጻ ትምህርት
ዕድል ስላገኘሁ የእንሰሳት ሐኪም (ዶክተር) በመሆን የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴንም አጠናቅቄአለሁ::
ጌታ ኢየሱስ ለመንግስቱ ሥራ እንደጠራኝ ሳረጋግጥ በጀርመን ጴንጤቆስጤ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት (BFP)
የሚሰጠውን የሦስት ዓመት የነገረ መለኮት ትምህርት ወስጄ በሴፕቴምበር 2010 በመጋቢነት ተሾሜአለሁ::
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ፍራንክፈርት ከተመሰረተችበት ከኤፕሪል 1990 ጀምሮ ጌታ በሰጠኝ ጸጋ
በታማኝነት ያገለገልሁ ሲሆን ከጃኗሪ 2012 ጀምሮ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንዋ መጋቢ በመሆን እያገለገልኩ
እገኛለሁ:: ቤተ ክርስቲያናችን በሽማግሌዎችና በመጋቢዎች ጥምረት በጋራ የምትመራ Team
Leadership ሲሆን ለአሰራር እንዲመች ሽማግሌዎቻችን ትኩረታቸው በአብዛኛው በአስተዳደሩ እና
በፋይናንሱ ላይ ነው:: መጋቢዎቹ ደግሞ በአብዛኛው የሚያተኩሩት መንፈሳዊው ሥራ ላይ ሲሆን
ማንኛውም ዓይነት ውሳኔ ግን የሚወሰነው በጋራ በመሆን ነው::
የውስጥ ረሃቤ እና ናፍቆቴ በቤተ ክርስቲያናችን የእግዚአብሔር ክብር ተገልጦ ብዙዎች እንዲድኑ፣ የዳኑት ደግሞ
እውነተኛ የየሱስ ደቀመዝሙር እንዲሆኑና ሁላችንም በጋራ በሐልዎቱ ውስጥ ሆነን በመንፈስና በእውነት ጌታን
እንድናመልክ ነው::
Belete Birehanu
Kinfe Birehanu
Kebede Tilahun
Zelalem Asfaw