(EECF) የወጣ አዋቂ ኮንፈረንሰ  ::

እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1

ወጣቶች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው ጸጋ እንዲበረቱና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እንዲያሳድጉ የተዘጋጀ ልዩ መድረክ ነው። "በጸጋ በርታ!" በሚለው መሪ ቃል፣ የእግዚአብሔር ጸጋ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን፣ በአገልግሎታችንና በግንኙነቶቻችን ውስጥ ያለውን የማይለካ ኃይልና ጥልቀት አብረን እንመረምራለን።

የሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የሰጠው ይህ ምክር፣ "ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ፣" ለዛሬው ትውልድ ወጣቶችም እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊ ጥሪ ነው። በዚህ ዓለም ፈተናዎች፣ ግራ መጋባቶችና ጫናዎች ውስጥ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ብቸኛው እውነተኛ የጥንካሬ፣ የመጽናናትና የተስፋ ምንጫችን ነው።

በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ወንድማችን ፓስተር አስፋው በቀለ ያገልግለናል:.

06.06.2025 (አርብ) ፡ 17:00 - 20:00 ሰዓት

07.06.2025 (ቅዳሜ) ፡ 10:00 - 13:00 ሰዓት & 14:30 - 17:30 ሰዓት

08.06.2025 (እሁድ) ፡ 10:00 - 13:00 ሰዓት & 15:00 - 18:00 ሰዓት

ቦታው ፡ Äthiopische Ev. Gemeinde Salzschlirfer Str. 7, 

60386 Frankfurt