13.04.2025
KUFTI )ኩፍቲ፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት እና ወጣቶች የፍራንክፈርት ሙዚየሞች እና Zoo መግቢያ
ኩፍቲ (የባህልና የመዝናኛ ቲኬት) የፍራንክፈርት ከተማ አስተዳደር ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት እና ወጣቶች በበርካታ የፍራንክፈርት ሙዚየሞች እና በፍራንክፈርት Zoo በነጻ ወይም በእጅጉ ቅናሽ የተደረገበት መግቢያ የሚያስችል አቅርቦት ነው። ዓላማው ወጣቶች የባህልና የመዝናኛ ቦታዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።
የ kufti.de/museen-zoo/ ድረ-ገጽ(Website) እንደ ማዕከላዊ የመረጃ መድረክ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፣ በዚህ ላይ ሁሉም ተሳታፊ ሙዚየሞች እንዲሁም የፍራንክፈርት Zoo በግልጽ ተዘርዝረዋል። ተጠቃሚዎች እዚህ ላይ በኩፍቲ (KUFTI) የትኞቹ የባህል ተቋማትና የመዝናኛ ቦታዎች መጎብኘት እንደሚችሉ በቀጥታ ማየት ይችላሉ። ስለዚህ ገጹ ለቤተሰቦች እና ለወጣቶች በፍራንክፈርት ሁለገብ የባህል ገጽታ ጉብኝታቸውን እንዲያቅዱ ተግባራዊ መመሪያ ይሰጣል።
ኩፍቲው ፍራንክፈርት ውስጥ ለሚኖሩ ወይም እዚህ ትምህርት ቤት ወይም የህጻናት መዋያ ለሚከታተሉ፣ ወርሃዊ የተጣራ ገቢያቸው ከ4,500 € (ዩሮ) በታች ለሆኑ ቤተሰቦች ልጆችና ወጣቶች በነጻ ነው። ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሌሎች ህጻናት እና ወጣቶች በሙሉ፣ የሚኖሩበት ቦታ ምንም ይሁን ምን፣ ቲኬቱ በዓመት 29 € (ዩሮ) ክፍያ ይገኛል።
ተጨማሪ መረጃዎችን እና ቲኬቱን ለማዘዝ የሚያስችል አማራጭ በቀጥታ በኩፍቲ ድረ-ገጽ ላይ ያገኛሉ። ስለ ተሳታፊ ተቋማት ዝርዝር መረጃ በ https://kufti.de/info/ ይገኛል።